Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

thrivebyfive

thrivebyfive
Mayor Muriel Bowser 

ትኩረታችን

 ትኩረታችን
Thrive by Five Framework

ታሪካችን

ዲስትሪክቱ ለእናቶች ጤና ብቻ ሳይሆን ለቅድመ ልጅነት ዕድገትና ትምህርት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ለማሳየት፣ ከንቲባ Bowser ለዲስትሪክቱ የመጀመሪያ አጠቃላይ የልጅነት ጤና እና የቅድመ ትምህርት ጅማሮ የሆነውን Thrive by Five DC በይፋ አስጀምረዋል። በሚያዝያ 2019 Thrive by Five DC Dr. Faith Gibson Hubbard የጽ/ቤቱ የመጀመሪያ ኤግዚኪዩቲቭ ዳይሬክተር አድርጎ የሾመ ሲሆን ከኦንላይን የመረጃ ማዕከልነቱ ከፍ ያለ ዕድገትም አሳይቶ ነበር።

እሴቶቻችን

በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ለሚገኙ ሁሉም ልጆች በት/ቤትና በሕይወታቸው ላይ ጠንካራ ጅማሮ እንዲኖራቸው፣ Thrive by Five በሚከተሉት እሴቶች የሚመራ ይሆናል፦

  • የዕድል ክፍተቱን ለመሙላት የልጆችና ቤተሰቦች እኩልነትና ተደራሽነት ላይ ትኩረት ማድረግ ወሳኝ ነው።
  • ወላጆች የልጃቸው የመጀመሪያ መምህርና በጣም ጠቃሚ ደጋፊ ናቸው።
  • የቅድመ ልጅነት ዕድገት ከቅድመ ትምህርት በላይ ሲሆን፣ አጠቃላይ የሆነ አቀራረብን ይጠይቃል።
  • የሚሳተፉ፣ የሚደገፉና የተሳሰሩ ማህበረሰቦች ለጤናማና የተቀናጀ የቅድመ ትምህርት ስርዓት ወሳኝ ናቸው።
  • እውነተኛ የሆኑ አጋርነቶችም ለእመርታና ለስኬታማነት አስፈላጊ ናቸው።

Thrive by Five የስራ ቡድን

Thrive by Five ዋና ዋና ግቦች መካከል ነባር ጥረቶችን በማስተባበርና በማቀናጀት የቅድመ ወሊድ ጤና እና ደህንነትን እንዲሁም የቅድመ ልጅነት ዕድገትና ትምህርት ጉዳይን መፍታት ይገኙበታል። Thrive by Five ራዕይን በአሁኑ ጊዜ እየተሰራ ካለው ስራ ጋር ለማስተሳሰር፣ Thrive by Five በጤና እንክብካቤና በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያሉና የቤተሰቦች ማነቆ፣በሁለቱ ስርዓቶች መገናኛ ላይ የፈጠረና የአዎንታዊ ውጤቶች ምሳሌዎች ተደርገው የሚቆጠሩ ወሳኝ ጉዳዮችና አዝማሚያዎችን እንደዚሁም የጎሉ ክፍተቶችን በመለየት ላይ የሚሰሩ ኤጄንሲዎችና ድርጅቶችን ያቀፈ አማካሪ ቡድን አሰባስቧል። የታሰበበት አጋርነት ከማቅረብ በተጨማሪ፣ Thrive by Five የስራ ቡድን የጽ/ቤቱ ስራ በሚገባ መከናወኑን ለማረጋገጥ ያግዛል።

የሚከተሉት ድርጅቶች Thrive by Five የስራ ቡድን ውስጥ የተወከሉ ናቸው፡