ታሪካችን
ዲስትሪክቱ ለእናቶች ጤና ብቻ ሳይሆን ለቅድመ ልጅነት ዕድገትና ትምህርት ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ለማሳየት፣ ከንቲባ Bowser ለዲስትሪክቱ የመጀመሪያ አጠቃላይ የልጅነት ጤና እና የቅድመ ትምህርት ጅማሮ የሆነውን Thrive by Five DC በይፋ አስጀምረዋል። በሚያዝያ 2019 ፣ Thrive by Five DC Dr. Faith Gibson Hubbard የጽ/ቤቱ የመጀመሪያ ኤግዚኪዩቲቭ ዳይሬክተር አድርጎ የሾመ ሲሆን ከኦንላይን የመረጃ ማዕከልነቱ ከፍ ያለ ዕድገትም አሳይቶ ነበር።
እሴቶቻችን
በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ለሚገኙ ሁሉም ልጆች በት/ቤትና በሕይወታቸው ላይ ጠንካራ ጅማሮ እንዲኖራቸው፣ Thrive by Five በሚከተሉት እሴቶች የሚመራ ይሆናል፦
- የዕድል ክፍተቱን ለመሙላት የልጆችና ቤተሰቦች እኩልነትና ተደራሽነት ላይ ትኩረት ማድረግ ወሳኝ ነው።
- ወላጆች የልጃቸው የመጀመሪያ መምህርና በጣም ጠቃሚ ደጋፊ ናቸው።
- የቅድመ ልጅነት ዕድገት ከቅድመ ትምህርት በላይ ሲሆን፣ አጠቃላይ የሆነ አቀራረብን ይጠይቃል።
- የሚሳተፉ፣ የሚደገፉና የተሳሰሩ ማህበረሰቦች ለጤናማና የተቀናጀ የቅድመ ትምህርት ስርዓት ወሳኝ ናቸው።
- እውነተኛ የሆኑ አጋርነቶችም ለእመርታና ለስኬታማነት አስፈላጊ ናቸው።
የ Thrive by Five የስራ ቡድን
የ Thrive by Five ዋና ዋና ግቦች መካከል ነባር ጥረቶችን በማስተባበርና በማቀናጀት የቅድመ ወሊድ ጤና እና ደህንነትን እንዲሁም የቅድመ ልጅነት ዕድገትና ትምህርት ጉዳይን መፍታት ይገኙበታል። የ Thrive by Five ራዕይን በአሁኑ ጊዜ እየተሰራ ካለው ስራ ጋር ለማስተሳሰር፣ Thrive by Five በጤና እንክብካቤና በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያሉና የቤተሰቦች ማነቆ፣በሁለቱ ስርዓቶች መገናኛ ላይ የፈጠረና የአዎንታዊ ውጤቶች ምሳሌዎች ተደርገው የሚቆጠሩ ወሳኝ ጉዳዮችና አዝማሚያዎችን እንደዚሁም የጎሉ ክፍተቶችን በመለየት ላይ የሚሰሩ ኤጄንሲዎችና ድርጅቶችን ያቀፈ አማካሪ ቡድን አሰባስቧል። የታሰበበት አጋርነት ከማቅረብ በተጨማሪ፣ የ Thrive by Five የስራ ቡድን የጽ/ቤቱ ስራ በሚገባ መከናወኑን ለማረጋገጥ ያግዛል።
የሚከተሉት ድርጅቶች በ Thrive by Five የስራ ቡድን ውስጥ የተወከሉ ናቸው፡
- AppleTree Early Learning Initiatives
- Bainum Foundation
- Bright Beginnings
- Children’s Law Center
- Community of Hope
- DC Action for Children
- DC Appleseed Center for Law & Justice
- DC Health Early Childhood Health Division, Community Health Administration
- DCPS Early Childhood Division
- DCPS Early Stages
- Educare DC
- Georgetown University, Early Childhood Innovation Network
- Loving Care Child Development Center
- Mamatoto Village
- Mary’s Center
- OSSE Division of Early Learning
- Petit Scholars
- Raise DC
- Spanish Education & Development Center
- United Planning Organization
- Washington Area Women’s Foundation